የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ የአፍሪካዊያን የስኬታማዎች ሽልማት አሸናፊ ሆኑ

ሐምሌ 8/2015 (ዋልታ) በ13ኛው ዓመታዊ የአፍሪካ አሸናፊዎች ሽልማት የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በእንግሊዝ ለንደን ውስጥ በተካሄደው የአፍሪካዊያን የስኬታማዎች ሽልማት (African Achievers Award) አሸናፊ ሆኑ።

ሽልማቱ ኢጋድ በአካባቢው ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ላደረገው አስተዋፅኦ መሆኑም ተገልጿል።

ሸላሚ ድርጀቱ ሽልማቱ ለስኬታማ ተግባር የተሰጠ ዕውቅና መሆኑን አስታውቋል።

ከብዙ የኢጋድ ስኬቶች ውስጥ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት እንዲሳካ የተደረገው ጥረት የሚጠቀስ መሆኑም ተመላክቷል ።

የአፍሪካ አሸናፊዎች ሽልማት ለአህጉሪቱ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅዖ ለሚያደርጉ አፍሪካ ውስጥ ላሉ ታዋቂ ግለሰቦችና ድርጅቶች እውቅና በመስጠት እና በማክበር የአፍሪካን የላቀ ደረጃ የሚያከብር ዓመታዊ የሽልማት ሥነ ሥርዓት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።

ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ትናንት ሐምሌ 7 ቀን 2015 ምሽት በተከናወነ የእውቅና ሥነ ሥርዓት ሽልማታቸውን ተረክበዋል።