የኦልማ የገቢ ማሰባሰቢያ የማጠቃለያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው

ግንቦት 27/2013 (ዋልታ) – የኦሮሚያ ልማት ማህበር የገቢ ማሰባሰቢያ የማጠቃለያ መርሃ ግብር በአንድነት ፓርክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እንደ ሀገር ኢትዮጵያ ከፍ ማድረግ አለብን ይህን ለማድረግ ደግሞ ሁላችንም በጋራ መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በበኩላቸው አሁን ሀገሪቱ የገጠማትን ፈተና ለማሸነፍ መልማት ግድ የሚለን ጊዜ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝደንት አኪንውሚ አዴሲ ኢትዮጵያ የአንድነት መገለጫ የአፍሪካ መዲና ማሳያ መሆኗን ገልጸው፣ ልማት ባንኩ የግብርና ትራንስፎርሜሽን፣ የኢንዱስትሪ ፓርክ ልማት እንዲሁም የስነ ምግብ ስራዎችን ያከናዉናል ብለዋል፡፡

(በሰለሞን በየነ)