የኮሌራ ወረርሽኝ በኦሮሚያ አምስት ወረዳዎች ተከሰተ


መጋቢት 20/2015 (ዋልታ)
የኮሌራ ወረርሽኝ በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ በባሌ፣ በምስራቅ ባሌ፣ በጉጂ እና በአዲሱ የምስራቅ ቦረና ወረዳ እየተስፋፋ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ ገልጿል።

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መንግስቱ በቀለ በአሁኑ ወቅት የበሽታው ምልክት በክልሉ በ17 ወረዳዎች እና በአንድ ከተማ ታይቷል ብለዋል።

ማቅለሽለሽ ፣ ማስታወክ ፣ የድካም ስሜት እና ከባድ የሆድ ድርቀት የኮሌራ ታማሚዎች ከሚያሳዩአቸው ምልክቶች መካከል ይጠቀሳሉ።

የቢሮ ኃላፊው የበሽታውን መነሻ ለማወቅና ስርጭቱን ለመቆጣጠር ሁሉንም ባለድርሻ አካላት የማሳተፍ ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በሽታው የተለያዩ አይነቶች እንዳሉት የገለፁት ዶ/ር መንግስቱን ህብረተሰቡ በአካባቢ ጥበቃና ንፅህና ላይ እንዲጠናከር እና ዘላቂ መፍትሄ ላይ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

መምሪያው እስካሁን በባህሪ ለውጥ ላይ የተለያዩ ስልጠናዎችን ሲሰጥ የቆየ ሲሆን የኮሌራ በሽታን ለመከላከል የህብረተሰቡ ግንዛቤ ዘላቂ መፍትሄ እንደሚያመጣም ገልጿል።

እንደ በተፈጥሮ አደጋ የሚመጣ ረሀብ እና የጸጥታ ችግሮች በክልሉ በሽታውን ለመቆጣጠር ዋነኛ ተግዳሮቶች ናቸው ሲል ቢሮው ገልጿል።

በሽታውን በቀዳሚነት ለመከላከል በኦሮሚያ እስካሁን ከ76 ሺሕ በላይ ሰዎች የኮሌራ ክትባት ተሰጥቷቸዋል።

በተለይም በሽታውን ለመዋጋት እና ድጋፍ ለመስጠት የጤና መዋቅሮች ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ በሽታውን ለመቆጣጠር የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ሲሆን በአገር አቀፍ ደረጃም የተለያዩ የድጋፍ ክትትል ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡

የኮሌራ ወረርሽኝ በምግብ እና በውሃ ብክለት ምክንያት የሚከሰትና በንፅሕና ጉድለት በፍጥነት የሚዛመት የበሽታ ዓይነት ነው።

በቡላ ነዲ