የኮሮናቫይረስ ክትባት ተፈትሾ 50.4 በመቶ ብቻ ውጤታማ መሆኑ ተገለፀ

ቻይናው ሲኖቫክ የተመረተው የኮሮናቫይረስ ክትባት በብራዚል ቤተሙከራዎች ውስጥ ተፈትሾ 50.4 በመቶ ብቻ ውጤታማ መሆኑ ተገለፀ።

የዚህ ክትባት ውጤታማነት ከዚህ ቀደም ይፋ በተደረገው መረጃ ከፍ ያለ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን የብራዚል ተመራማሪዎች 50 በመቶን ያለፈው ለጥቂት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የብራዚል መንግሥት ለዜጎቹ ለመስጠት ካዘጋጃቸው ሁለት ክትባቶች መካከል የቻይናው አንዱ ነበር።

ብራዚል በኮሮናቫይረስ ክፉኛ ከተጠቁ አገራት መካከል አንዷ ናት። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)