የውጭ አገራት ጣልቃ ገብነት የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በዲላ ከተማ ተካሄደ

ግንቦት 25/2013 (ዋልታ) – በጌዴኦ ዞን በዲላ ከተማ በተካሄደው በሰላማዊ ሰልፍ ላይ ከ20 ሺህ ሕዝብ የሚሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎቸ በአደባባይ  ተቋውሞአቸዉን አስምተዋል ።

በሰላማዊ ሰልፍ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሽፈራዉ ቦጋለ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ነጻነቷንና ክብሯን ጠብቃ የኖረች ሀገር በመሆኗ አሁን በዉጭ ሀገር ጣልቃ ገብነት እየተካሄደ ያለው ጫና ተቀባይነት የሌለው ነዉ ብለዋል ።

በተለይ ወጣቱ ትዉልድ በአሁኑ ሰዓት አንድነቱን በማጠናከር በሀገር የተጀመረውን ለዉጥ በዘላቂነት ለማስቀጠል ከዉጭ ሀገር የሚናፈሰዉን ወሬ ወደ ጎን በመተው ዛሬ ላይ በትጋት መስራት አለበት ብለዋል ።

የጥንት አባቶቻችን የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ጠብቀው በማቆየት ለዚህ በማብቃታቸው እኛም የሀገር ክብርና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ በትጋት መስራት ይጠበቅብናል ማለታቸዉን የዘገበው የጌዴኦ ዞን የመንግሰት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መመሪያ ነው።