የዓለም ቱሪዝም ወደ ቅድመ ኮሮና ለመመለስ ጠንካራ ማገገም እየታየበት መሆኑ ተጠቆመ


መስከረም 9/2016 (አዲስ ዋልታ) የዓለም ቱሪዝም ከኮረና ወረርሽኝ በፊት ወደ ነበረበት ደረጃ ለመድረስ ጠንካራ የማገገም ሂደት ላይ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በፈረንጆቹ ከጥር እስከ ሐምሌ 2023 ባለው ጊዜ የጎብኝዎች ቁጥር 84 በመቶ መድረሱን የተባበሩት መንግስታት የቱሪዝም ድርጅት (UNWTO) ባወጣው ጥናት አስታውቋል፡፡

ጥናቱ እንደሚያሳው የጎብኝዎች ቁጥር እ.ኤ.አ ታህሳስ 2019 ወደ ነበረበት ደረጃ ለመመለስ መቃረቡ ነው የተጠቆመው፡፡

የጥናት ውጤቱ እንዳመለክተው በተጠቀሰው ሩብ ዓመት በመካለኛው ምስራቅ (120 በመቶ) በአውሮፓ (በ91 በመቶ) እና በአፍሪካ (92 በመቶ) ከፍተኛ መሻሻል ያሳዩ የዓለም ክፍሎች መሆናቸውም ተጠቅሷል፡፡

በተለይ መካከለኛው ምስራቅ በኮሮና ወረርሽን ወቅት ከነበረው የቱሪስት ፍሰት አልፎ የ20 ከመቶ ጭማሪ ያሳየ ብቸኛው የዓለም ክፍል ሆኗልም ተብሏል፡፡

በአንጻሩ እስያና አሜሪካ ዝግ ያለ ማገገም የያሳዩ ሲሆን የጎብኝዎች ቁጥር በቅደም ተከተል 61 እና 87 በመቶ ብቻ መሆኑ በመረጃው ተመላክቷል፡፡

በነዚህ ሶስት ወራት ከ700 ሚሊዮን በላይ ቱሪስቶች ዓለምን የጎበኙ ሲሆን ከባለፈው ተማሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር የ43 ከመቶ ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል፡፡

በሀምሌ 2023 ብቻ 145 ሚሊዮን ቱሪስቶች ጉብኝት ማደረጋቸው በጥናቱ ተገልጿል፡፡

የበጀት ዓመቱ የመጨረሻ ሩብ ዓመት አጠቃላይ የጎብኝዎች ቁጥር እንደሚጨምርና ዕድገቱ ከ80-95 በመቶ ሊደርስ እንደሚችል ተገምቷል፡፡

ለዘርፉ ጠንካራ ማገገም ደግሞ ቻይና እና ሌሎች የእስያ አገሮች ጎብኝዎችን ለመቀበል በራቸውን ክፍት ማድረጋቸውና ከፍተኛ የአየር ትራንስፖርት ትስስር መፈጠሩ እንደዋና አስቻይ ሁኔታዎች ተጠቅሰዋል፡፡

በሌላ በኩል የዘርፉን የማገገም ጥረት ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ማነቆዎች በተለይም የዋጋ ግሽበት የነዳጅ ዋጋ ማሸቀብ እና የጸጥታ ሁኔታች ሊያጓትቱት እንደሚችል በመረጃው ተጠቁሟል፡፡