የዓለም ፍልሠተኞች ድርጅት 1 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር የሚገመት የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

መስከረም 5/2015 (ዋልታ) የዓለም ፍልሠተኞች ድርጅት 1 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር የሚገመት የሕክምና ቁሳቁስ ለኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ድጋፍ አድርጓል።

ኢንስቲትዩቱ ከዓለም ፍልሰተኞች ድርጅት ለአገልግሎት የሚያግዙትን ድጋፎች ማግኘቱን ገልጿል።

በዚህም 1 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር የሚገመት የመድሃኒትና የህክምና ግብዓቶች ከድርጅቱ ማግኘቱን ነው ያስታወቀው።

ድጋፉን በቦሌ አለም ዓቀፍ አየር ማረፊያ ለተጓዦች የጤና አገልግሎት እና የልየታ ስራ የሚያከናውን መለስተኛ ክሊኒክ በማዘጋጀት አስረክቧል።