አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለተጨማሪ ሁለት አመታት ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር ለመቆየት ውሉን አራዘመ

መስከረም 5/2015 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለተጨማሪ ሁለት አመታት ከብሄራዊ ቡድኑ ጋር ለመቆየት ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በዛሬው ዕለት ስምምነት ፈፅሟል።

በ2013 ዓ.ም ብሔራዊ ቡድኑንን በመረከብ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በስራ ላይ የቆየው አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በቆይታው ብሔራዊ ቡድኑ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ከስምንት ዓመት በኋላ እንዲመለስ አስችሏል።

በቅርቡ ደግሞ በአልጄርያ ለሚከናወነው የአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮንሺፕ (ቻን) ቡድ ከስድስት ዓመታት ቆይታ በኋላ የውድድር ተሳትፎን አሳክቷል።

የአሰልጣኙ ውል መጠናቀቁን ተከትሎም ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት (እስከ መስከረም 2017 ዓ.ም) ድረስ በዋና አሰልጣኝነት እንዲቀጥል በዛሬው ዕለት የውል ስምምነት መፈራረማቸውን የፌዴሬሽኑ መረጃ ያመለክታል።