የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መግቢያ ውጤት ይፋ ሆነ

መጋቢት 30/2013 (ዋልታ) – የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሀገር አቀፍ ማጠቃለያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎችን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተማሪዎች የወንዶች መግቢያ 380 እና ከዛ በላይ ለሴቶች ደግሞ 368 እና ከዛ በላይ ያስመዘገቡ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግባት ይችላሉ ብሏል።

ለታዳጊ ክልሎች የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት 368 እና ከዛ በላይ ውጤት ያመጡ ወንድ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ይገባሉ፡፡

በተጨማሪም በትግራይና መተከል የመደበኛ ተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ለወንድ 358 እና ከዛ በላይ፣ ለሴቶች ደግሞ 350 እና ከዛ በላይ ማለፊያ ውጤት ሆኗል፡፡

ለማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ደግሞ የ2013 መግቢያ ውጤት ለወንዶች 370 እና ከዛ በላይ ለሴቶች ደግሞ 358 እና ከዛ በላይ መሆኑን አስታውቋል።

ለታዳጊ ክልል ወንድ ተማሪዎች መግቢያ ውጤት 358 እንደሆነና ለሴቶች 348 እንደሆነ በመግለጫው ተጠቁሟል።

የትግራይና የመተከል ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ለወንድ 348 ለሴት ደግሞ 340 ማለፊያ ውጤት ነው ተብሏል።

ማየት ለተሳናቸው እንዲሁም መስማት ለተሳናቸው የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች መግቢያ ውጤት ለወንድ 348 ለሴት ደግሞ 340 መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም መደበኛ ላልሆኑ ፕሮግራሞች ለወንድ 330 እና ከዛ በላይ ለሴት ደግሞ 320 እና ከዛ በላይ መግቢያ ውጤት ሆኗል።

የግል ተቋም የህክምና ሳይንስ ለሁሉም ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት 450 ሆኗል ነው የተባለው፡፡

በአጠቃላይ 147ሺ 640 ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ቅበላ እንደሚደረግላቸው ተገልጿል፡፡

(በሱራፌል መንግስቴ)