የዩክሬን ፕሬዝዳንት በእንግሊዝ ጉብኝት እያደረጉ ነው

የካቲት 1/2015 (ዋልታ) የየክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ዛሬ እንግሊዝ መግባታቸው ተገለጸ፡፡

ለፕሬዝዳንቱ የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ በለንደን የስታንስቴድ አየር ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ወደ ዳውኒንግ ስትሪት በመጓዝ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ውይይት እንደሚያደርጉ አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

በጉብኝታቸው ለእንግሊዝ የፓርላማ አባላት ንግግር እንደሚያደረጉ እንዲሁም ከሳልሳዊ ንጉስ ቻርልስ እና ከፍተኛ የጦር አለቆች ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩ ተመላክቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በእንግሊዝ የዩክሬን ጦር ማሰልጠኛን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል፡፡

የፕሬዝዳንቱ ጉዞ ዩክሬን ከሩስያ ጋር ጦርነት ውስጥ ከገባች ወዲህ ወደ ውጭ ሲጓዙ ሁለተኛው እንደሆነ ዘገባው አስታውሷል፡፡