የዲያስፖራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ እና የአረብኛ ሚዲያዎች ሚና በሚል ውይይት እየተካሄደ ነው

ግንቦት 17/2014 (ዋልታ) የዲያስፖራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ እና የአረብኛ ሚዲያዎች ሚና በሚል የውይይት መድረክ እና አውደ ርዕይ እየተካሄደ ነው።

ኢትዮጵያ ላለፉት ጊዜያት ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጫና በተለይም የተፈጥሮ ሀብቶቿን ለመጠቀም በምታደርገው እንቅስቃሴ ጫናዎች ብርትተውባት ቆይቷል፡፡

ሆኖም ሀገሪቱ በኢትዮጵያዊያን ብርቱ ትግል እና በዲያስፖራው ጥረት ይህን ጫና እየቀለበሰች በዋናነትም ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በተመለከተ በአረቡ ዓለም ትልቅ የዲፕሎማሲ ሥራ ሲሰራ መቆየቱ ተመላክቷል፡፡

አሁንም በአረቡ ዓለም የኢትዮጵያን በሕዳሴ ግድብ ላይ ያላትን የፍትሃዊ ተጠቃሚነት አቋም ለማስረዳት በዲያስፖራው ፐብሊክ ዲፕልማሲ፣ በአረብኛ ሚዲያዎች እና በሕዝብ ለሕዝብ ውይይቶች ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ገልፀዋል።

የዚሁ አካል የሆነው ከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት ጥሪ ትልቅ ውጤት የታየበት ሲሆን ምዕራፍ ሁለት በቅርቡ ይጀምራልም ነው የተባለው።

በሜሮን መስፍን

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW