የድሬዳዋ ስፖርት አካዳሚ ግንባታ 97.7 በመቶ ደረሰ

የድሬዳዋ ስፖርት አካዳሚ

መጋቢት 21/2015 (ዋልታ) የድሬዳዋ ስፖርት አካዳሚ አፈፃፀም 97 ነጥብ 7 በመቶ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ።

የአካዳሚው የስፖርት ፋሲሊቲ ቡድን መሪ ምህረቱ ዘላለም አካዳሚው ለ120 ሰልጣኞች ማረፊያ፣ አዳራሽ፣ የቤት ውስጥ የመዋኛ ገንዳ፣ የእግር ኳስ ሜዳና መሰል የስፖርት ማዘውተሪያዎች እንዲይዝ ተደርጎ እየተገነባ መሆኑን ገልጸዋል።

በድሬዳዋ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን እየተገነባ የሚገኘው አካዳሚው በዘንድሮ ዓመት ግንባታው ተጠናቆ በቀጣይ ዓመት ወደ ስራ እንደሚገባም ተጠቁሟል፡፡

ለስፖርት አካዳሚው ግንባታ 307 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታልም ነው የተባለው።

አካዳሚው ድሬዳዋ ከዚህ ቀደም በስፖርት የነበረባትን እውቅና ወደ ቀደመ እንዲመልስ ተስፋ የተጣለበት ነውም ተብሏል።

ሰለሞን በየነ (ከድሬዳዋ)