የድንገተኛ አደጋ እና ፅኑ ህክምና አገልግሎት ለማሻሻል የሚያስችል ስምምነት

መስከረም 7/2014 (ዋልታ) የጤና ሚኒስቴር የድንገተኛ አደጋ እና የፅኑ ህክምና አገልግሎት ለማሻሻል ከፖሊሽ ሴንተር ፎር ኢንተርናሽናል ኤይድ መካከል ለሦስት ዓመት የሚቆይ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመናል፡፡

የተፈረመው ሰነድ ለአንቡላንስና ድንገተኛ አደጋ ህክምና የሚውሉ ግብዓቶችን ማቅረብ፣ ለድንገተኛ ህክምናና ፓራሜዲክ ባለሙያዎች ስልጠና፣ የቅድመ ጤና ተቋም አገልግሎትን ለማሳለጥ የጥሪ እና ስምሪት ማዕከል ማጠናከር፣ ለትራፊክ እና በጅምላ ለሚደርሱ አደጋዎች ምላሽ አሰጣጥን የሚያሻሽሉ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎችን ያካትታል ተብሏል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው እንዳስታወቁት፣ ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ በፖላንድ መንግስት የሚደገፍ ሲሆን፣ ጠንካራ የጤና ስርዓት ለመገንባት ላቅ ያለ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ይጠበቃል፡፡

ሚኒስትሯ ለድጋፉ የፖላንድ መንግሥት እንዲሁም የፖላንድ ለዓለም አቀፍ ዕርዳታ ማእከልን አመስግነዋል።