የጃፓኑ ሱምቶም በኢትዮጵያ ከ2 ቢሊየን ዶላር በላይ በቴሌኮም ዘርፍ ኢንቨስት እንደሚያደርግ አስታወቀ

ሰኔ 01/2013 (ዋልታ) – የጃፓኑ ሱምቶም በኢትዮጵያ ከሁለት ቢሊየን ዶላር በላይ በቴሌኮም ዘርፍ ኢንቨስት እንደሚያደርግ አስታወቀ።

በቴሌኮም ዘርፍ የውጭ ባለሀብቶች እንዲሳተፉ መንግስት በወሰደው ውሳኔ መሠረት  ጨረታውን ያሸነፈው ‘የግሎባል ፓርትነርሽፕ ፎር ኢትዮጵያ‘ ድርጅት  አንዱ የሆነው የጃፓኑ ሱምቶም በቀጣይ አምስት ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ ከሁለት ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳለው የኮርፖሬሽኑ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ  አስታውቀዋል፡፡

የኮርፖሬሽኑ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ቶሽካዙ ናምቡ የኢንቨስትመንት ዕቅዳቸውን ያስታወቁት በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር ካሣ ተክለብርሃን ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡

ምክትል ሥራ አስፈጻሚው ኮርፖሬሽናቸው ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን  የኢትዮጵያ መንግስት በግልጸኝነት ባካሄደው የጨረታ ሂደት በማሸነፋቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡

አምባሳደር ከሳ ተክለብረሃን በበኩላቸው፣ ኮርፖሬሽኑ በጃፓን፣ በኤሽያ እና በአፍሪካ ያለው የካበተ ልምድ በኢትዮጵያ ኢንቨስት በማድረግ እንዲደግመው ጥሪ ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛው የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችን
የአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛው የትዊተር ገፃችን
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!