የጅቡቲ ብሄራዊ ፖሊስ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲን ጎበኙ

የጅቡቲ ብሄራዊ ፖሊስ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የስራ ጉብኝት አደረጉ።

የጅቡቲ ብሄራዊ ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር ኮሎኔል አብዱላሂ አብዲ ፋራህ እና የጅቡቲ ብሄራዊ ፖሊስ የመረጃ ደህንነትና ኢምግሬሽን ሀላፊ ኮሎኔል አብዱልቃድር ኢብራሂም በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ም/ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን አበበ ፣ምክትል ፕሬዝደንቶች እና ሌሎች የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ጉብኝት አድርገዋል፡፡

ስለ ዩኒቨርሲቲው አጠቃላይ ገፅታ ገለጻ የተደረገላቸው ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙትን ቤተ-መፅሀፍትን፣ ቤተ-መዘክር እንዲሁም አዲስ የተገነባውን የዩኒቨርሲቲውን ግቢ መጎብኘታቸውን ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።