የጉለሌ ክፍለ ከተማ ግንባታቸው የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን አስመረቀ

መጋቢት 9/2014 (ዋልታ) የጉለሌ ክፍለ ከተማ ከ27 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የተገነቡ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን አስመረቀ።

ክፍለ ከተማው በከተማ ልማታዊ ሴፍቲ ኔት ፕሮጀክቶች በአጠቃላይ 84 የሚሆኑ የጋራ መፀዳጃ እና ሻዎር ቤቶች አስመርቋል።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱም የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ፣ የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቆንጂት ደበላ እንዲሁም የተለያዩ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በእመቤት ንጉሴ