የካቲት 11/2013 (ዋልታ) – የጌዴኦ ዞን የዘመን መለወጫ የሆነው የደራሮ በአል በዲላ ከተማ እየተከበረ ነው፡፡
ደራሮ በየአመቱ በጌዴኦ ባህላዊ የዘመን አቆጣጠር መሰረት ከታህሳስ ወር የመጨረሻዎቹ ቀናት አንስቶ እስከ ጥር አጋማሽ ካሉት ቀናት በአንዱ የሚከበር ነው፡፡
ወቅቱ አርሶ አደሩ የቡና የገብስ እና መሰል ምርቶቹን ሰብስቦ ለቀጣይ ምርት የሚሰናዳበት ነው።
የጌዴኦ አባ ገዳ አርሶ አደሩ ምርቱን፣ አዝመራና ሰብሉን ሰብስቦ መጨረሱን ካረጋገጡ በኋላ ቀኑን ባህላዊ አቆጣጠር የጨረቃና ከዋክብት መግባት መውጣቱን ደራሮን በይፍ ያውጃሉ።
ጌዴኦ በባህላዊው እና ህዝባዊው የባሌ አስተዳደር ስርአት በየስምንት አመቱ የሚቀያየር አባ ገዳ መርጦ የሚተዳደር ህዝብ ነው።
(በስመኝ ፈለቀ)