“የግሉ ዘርፍ ኢንቨስትመንት የምርታማነት ግባችንን ለማሳካት ወሳኝ ነው” – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ሰኔ 10/2014 (ዋልታ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የግሉ ዘርፍ ኢንቨስትመንት የምርታማነት ግብ ለማሳካት ወሳኝ ነው ሲሉ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህንን ያሉት በደቡብ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ ያደረጉትን ጉብኝት ተከሎ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ነው፡፡

“በግል ባለሀብቶች በወላይታ ሶዶ በ1 ሺሕ 250 ሄክታር መሬት ላይ በተከወነው ግብርና የተገኘው የፍራፍሬ ምርታማነት የሚደነቅ ነው” ሲሉ አክለዋል።