የግንባታ ግብዓቶች ዋጋ መናር ለኮንስትራክሽን ዘርፍ ተግዳሮት መሆኑ ተገለጸ

የግንባታ ግብዓቶች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መናር በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ሁለንተናዊ ቀውስ በመፍጠር ፕሮጀክቶች እንዲጓተቱ ምክንያት መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር በወቅታዊ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በአሁኑ ወቅት በተለይ በሲሚንቶና በአርማታ ብረት ላይ ያለው የዋጋ ንረት የፕሮጀክቶችን ግንባታ እንዲቆም በማድረግ ሀገሪቱን ወደ ችግር ውስጥ እያስገባት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በተለያዩ መንግስታዊ ግዢ ፈፃሚ መሥሪያ ቤቶች በኩል የሚታዩ ኢ-ፍትሐዊ የግንባታ አገልግሎት ግዢ አፈፃፀም ሂደቶች ዘርፉን እየተፈታኑት ነውም ተብሏል፡፡

በተጨማሪም በባንኮች በኩል እየተተገበሩ ባሉ የአሠራር ሥርዓቶች ምክንያት በግንባታ ተቋማት ላይ እየተፈጠሩ ያሉ የአሠራር ማነቆዎች ተጨማሪ የዘርፉ እንቅፋቶች መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡

(በአካሉ ጴጥሮስ)