የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቃልኪዳን ቤተሰብ ትውውቅ መርሃግብር እየተካሄደ ነው


ጎንደር፣ ሐምሌ 25/2013 (ዋልታ) –
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቃልኪዳን ቤተሰብ ትውውቅ መርሃግብር እየተካሄደ ነው፡፡
ለሁለተኛ ዙር የሚካሄደው የቤተሰብ ትውውቅ መርሃግብር አዳዲስ የዩንቨርስቲው ተማሪዎችን ጎንደር ከሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ጋር ለማስተሳሰር ያለመ ነው፡፡
የቃልኪዳን ቤተሰብ ትስስር ፕሮጀክት ባሳለፍነው ዓመት የተጀመረ ሲሆን ዓላማው አዳዲስ ተማሪዎች ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተመድበው ሲመጡ የባይተዋርነት ስሜት ሳይሰማቸው ከጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ጋር ጥብቅ ትስስር የሚፈጥሩበትና ለአንድ አዲስ ተማሪ አንድ ወላጅ (ቤተሰብ) የሚያገናኝ የቤተሰብ ፕሮጀክት ነው፡፡
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቤተሰብ ትውውቅ ባሳለፍነው ዓመት 5000 ሺህ ተማሪዎችን ከጎንደር ከተማ ቤተሰቦች ጋር አስተሳስሯል፡፡
(በሳሙኤል ሀጎስ)