የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርኃ ግብር በሠላም ተጠናቀቀ

የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርኃ ግብር

ሚያዝያ 22/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ ከተማ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የተዘጋጀው የጎዳና ላይ ታላቅ የኢፍጣር መርኃ ግብር ያለ አንዳች የፀጥታ ችግር መጠናቀቁን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል፡፡

ለመርኃ ግብሩ በሠላም መጠናቀቅ አስተዋፅኦ ያደረጉትን ለመላው የከተማዋ ነዋሪዎች እና ሁልጊዜም የተሰጠውን ሠላምና ደኅንነት የማረጋገጥ ኃላፊነት በሙሉ ቁርጠኝነት ለሚወጣው የፀጥታ ኃይል እንዲሁም ለሕዝበ ሙስሊሙ የጋራ ግብረ ኃይሉ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

መላው የከተማዋ ነዋሪዎች በመቻቻልና በመከባበር ጠብቆ ያቆያቸውን መልካም እሴቶችም አጠናክሮ በመቀጠል ለከተማዋ ሠላም የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያበረክትም ጥሪ መቅረቡን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ አመላክቷል።

 

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!