የጠቅላይ ሚኒስትሩን የፓርላማ ንግግር የያዘ ”አሻራ” የተሰኘ መጸሐፍ የምርቃት ስነስርአት እየተካሄደ ነው

ግንቦት 30/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ባለፉት ሶስት አመታት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያደረጓቸውን ንግግሮች የያዘው ”አሻራ” የተሰኘ መፅሃፍ የምርቃት ስነስርአት እየተካሄደ ነው።

እንደ ኢዜአ ዘገባ መጽሐፉ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የተዘጋጀ ሲሆን ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን በምክር ቤቱ ያደረጉትን ንግግር በመያዝ ለንባብ በቅቷል።

በምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።