የጣይቱ ባህልና ትምህርት ማዕከል የትውውቅና የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃግብር እየተካሄደ ነው

መጋቢት 4/2013 (ዋልታ) – የጣይቱ ባህልና ትምህርት ማዕከል የትውውቅና የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃግብር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በመርሃ ግበሩ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ጨምሮ  ሚኒስትሮችና  የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።

በታዋቂና ከያኒ አለምጸሃይ ወዳጆ የተመሰረተው ጣይቱ የባህልና ትምህርት ማዕከል ላለፉት 20 ዓመታት በሰሜን አሜሪካ በኪነ-ጥበብና በትምህርት ላይ ሲሰራ እንደነበር ይታወቃል።

ማዕከሉ በተለያዩ የአለም ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሀገራቸውን ባህልና ቋንቋ በማስተዋወቅ በኩል ጉልህ ሚና መጫወቱን ኢዜአ ዘግቧል።

በቅርቡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዛሬ 117 ዓመት ተገንብቶ በቅርስነት የተመዘገበውን የቢትወደድ ሃይለጊዮርጊስ ወልደሚካኤልን መኖሪያ ቤት ለጣይቱ ባህልና ትምህርት ማዕከል አስረክቧል።