የኮቪድ-19 ክትባት በኦሮሚያ ክልል ሞጆ ከተማ መስጠት ተጀመረ

መጋቢት 4/2013 (ዋልታ) – የኮቪድ-19 ክትባት በኦሮሚያ ክልል ሞጆ ከተማ የሞጆ ፕራይመሪ ሆስፒታል ዛሬ መሰጠት ተጀምሯል።

በክትባት ማስጀመሪያው መርኃግብር የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ሎሚ በዶ እንዲሁም የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መንግስቱ በቀለ ተገኝተዋል፡፡

ክትባቱ ለጤና ባለሙያዎች እንዲሁም ተጓዳኝ የጤና ህመም ላለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ቅድሚያ እንደሚሰጥ ታውቋል።

ወደ ሀገሪቱ ከገባ ጀምሮ በሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ሕይወት የቀጠፈው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የስርጭት ሁኔታ አሁንም አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመሆኑ በሽታውን ለመከላከል የሚደረገው ጥንቃቄ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገልጿል።