የፀሎተ ሀሙስ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በተለያዩ ሥነ -ሥርዓቶች ተከበረ

ሚያዝያ 5/2015 (ዋልታ) የፀሎተ ሀሙስ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የኢየሱስ ክርስቶስን ትህትና በማሰብ በተለያዩ ሥነ-ሥርዓቶች እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም እየተከበረ ሲሆን እየሱስ ክርስቶስ በዛሬዋ እለት የሃዋርያትን እግር ዝቅ ብሎ በማጠብ ትህትናን እና ታዛዥነት ማስተማሩን በማሰብ የሚደረገው የህፅበተ እግር ሥነ-ሥርዓትም እየተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ ብፁዓን ጳጳሳት፣ ቆሞሳት፣ ካህናት እና በርካታ ምዕመናን በተገኙበት ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቱ እየተከናወነ ይገኛል።