ከተማ አስተዳደሩ ከ256 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የሀገር ባለውለታዎችና አቅመ ደካሞች ማዕድ አጋራ

ሚያዝያ 5/2015 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትንሳዔ እና የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ከ256 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የሀገር ባለውለታዎች፣ አቅመ ደካሞች እንዲሁም ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች ማዕድ አጋራ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ 555 የአቅመ ደካማ ቤቶችንም አድሰን አስረክበናል ብለዋል፡፡
ባለሀብቶችንና ነዋሪዎችን አስተባብረን ለነዋሪዎቾቻን ማዕድ ስናጋራ ያለንን ፍቅር እና አክብሮት እንዲሁም ቃል በገባነው መሠረት ዝቅ ብለን እያገለገልን መሆናችንን በተግባር የምናሳይበት ነው ብለዋል።
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ‘መስጠት አያጎድልም’ ብለው ካላቸው ቀንሰው ለወገኖቻችን ማዕድ እንድናጋራ ላገዙን ልበ-ቀና ባለሀብቶች፣ ነዋሪዎች እና በጎ ፍቃድ አገልጋዮችን አመስግነዋል፡፡