የፀደይ ባንክ መሰራች ጉባኤ ተካሄደ

መጋቢት 25/2013 (ዋልታ) – የፀደይ ባንክ የባለአክስዮኖች መመስረቻ ጠቅላላ ጉባዔ በባህርዳር ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
በተከፈለ ስምንት ቢሊዮን ብር በሚጠጋ ካፒታል በምስረታ ላይ የሚገኘው ባንኩ ከ793 ሺሀ በላይ አባላት እንዳሉትም ተገልጿል፡፡
የቀደሞው የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም /አብቁተ/ ስያሜውን ወደ ፀደይ ባንክ በመቀየር የአገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋና ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ የሚንቀሳቀስ መሆኑን የተቋሙ የሥልጠናና ምርምር ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተዋበ አይሸሹም አስታውቀዋል፡፡
እንደ ኢዜአ ዘገባ በመመስረቻው ጠቅላለ ጉባዔ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ ሌሎች የፌደራልና ክልል የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ጠቅላላ ጉባዔውም የመተዳደሪያና የባንክ መመስረቻ ጽሁፍን ቀርቦ እንደሚፀድቅ እንዲሁም የቦርድ አባላት ምርጫ እንደሚካሄድ ይጠበቃል፡፡