የፌስቡክና ኢንስታግራም በመላው ዓለም አገልግሎት ተቋረጠ

በመላው ዓለም የሚገኝ የፌስቡክና ኢንስታግራም አካውንቶች መቋረጡ ተሰምቷል።

በዛሬው ቀን ከምሽቱ 12 ሰዓት አካባቢ ጀምሮ ፌስቡክ እየሰራ አለመሆኑን ከተለያዩ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ለማረጋገጥ ተችሏል።

አካውንቶቹ ሎግ አውት (log out) ተደርገው በራሱ ሰዓት የወጡ ሲሆን ዳግም መግባት እንዳልተቻለም ከተጠቃሚዎች የደረሰን መረጃ ያሳያል።

ፌስቡክ እስከ መቼ እንደሚቋረጥ የታወቀ ነገር የለም።

በዚሁ ዙሪያ አዳዲስ መረጃ ሲኖር ተከታትለን የምናደርሳችሁ ይሆናል።