የፌደራል ህብረት ስራ ኤጀንሲ የ10 አመት እቅድ ላይ ያተኮረ ውይይት ዛሬ ተጀመረ

                                                           የፌደራል ህብረት ስራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኡስማን ሱሩር

የፌደራል ህብረት ስራ ኤጀንሲ የ10 አመት እቅድ ላይ ያተኮረ ውይይት በሀዋሳ ከተማ ዛሬ ተጀምሯል፡፡

በመድረኩ የኤጀንሲውን የሪፎርም ስራዎች እና የ10 አመት እቅዱን ገቢራዊ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር እየተደረገ ነው።

የክልሎች የህብረት ስራ የስራ ሀላፊዎች እየተሳተፉ በሚገኙበት በዚሁ መድረክ ላይ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ኡስማን ሱሩር እንዳሉት በ2012 በጀት አመት የኮቪድ 19 ወረርሽኝን በመቋቋም አመርቂ ዉጤት ማስመዝገብ ተችሏል።

የሴክተሩን የ10 አመት   መሪ አቅድ ተፈፃሚ ለማድረግም ዘመናዊ የአሰራር ስርአትን መተግበር ይገባል ብለዋል።

የህብረት ስራ ሴክተር ተጨባጭ ውጤቶችን ማስመዝገብ ከቻለባቸው ስኬቶች መካከል የአባላትን ቁጥርና ካፒታል ማሳደግ   መቻሉን ለአብነት አንስተዋል።

በዘርፉ ለተመዘገበው ውጤት የሴክተሩ አካላት በቅንጅት መስራታቸው መሆኑንም ለአብነት አንስተዋል።

(በበሀይሉ ጌታቸው)