የአማራ ባንክ አ.ማ የውክልና ግዜው ተራዘመ

የአማራ ባንክ አ.ማ የውክልና ግዜው እስከ ታህሳስ 15 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ መራዘሙ ተገለጸ፡፡

የአክሲዮን ሽያጩን ህዳር 21 ቀን 2013 ሲያጠናቅቅ 8 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ቃል የተገባና 6 ቢሊዮን ብር ደግሞ የተከፈለ ካፒታል ማሰባሰብ መቻሉን የባንኩ አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ መላኩ ፈንታው ተናግረዋል፡፡

ጠቅላላ ጉባኤ ለመጥራት የባለአክሲዮኖች ቁጥር መብዛትና የኮሮና መመሪያ ጉባኤውን ማካሄድ የማይቻል በመሆኑ በውክልና ተሳታፊ እንዲሆኑ እየተደረገ ነው ተብሏል፡፡

በመሆኑም የውክልና ጊዜ ማራዘም እንደሚያስፈልግ ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም በኢንሹራንስ ዘርፍ ለመሰማራት ዝግጅት እያደረገ ስለመሆኑ ተገልፆ አለም አቀፍ ተደራሽ የሆነ ባንክ ለማድረግም ይሰራል ተብሏል፡፡

አማራ ባንክ አ.ማ 185 ሺህ ባለአክሲዮኖች እንዳሉት ተገልጿል፡፡

(በሰለሞን በየነ)