የፌዴራል ፖሊስ ልዩ ኮማንዶና የወንጀል ምርመራ ቡድን መቐለ ከተማ ገባ

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ልዩ ኮማንዶና የወንጀል ምርመራ ቡድን ዛሬ ህዳር 23 ቀን 2013 ዓ.ም መቐለ ከተማ መግባቱን አስታውቋል።

የፌዴራል ፖሊስ ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በመቀናጀት የጁንታውን ተፈላጊ ወንጀለኛ ቡድን ማደን መጀመሩ ተገልጿል።

የኮማንዶ ቡድኑ በከተማዋ በሚያደርጋቸው አሰሳዎችና የተለያዩ ኦፕሬሽኖች እንዲሁም በወንጀል ምርመራ ቡድኑ የሚገኙ ውጤቶችን በቀጣይ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግም ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡