ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከእስራኤል የኢሚግሬሽን ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የእስራኤልን የኢሚግሬሽን ሚኒስትር ፕኒና ቶማኖ ሻታን በቤተመንግሥት ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

ሚኒስትሯ ወደ ትውልድ አገራቸው ኢትዮጵያ በመምጣታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ግንኙነት ለማጠናክር እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

ፕኒና ቶማኖ ሻታ በእስራኤል ይህንን የስራ ኃላፊነት የያዙ የመጀመሪያዋ ትውልደ ኢትዮጵያዊት መሆናቸውን ከፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡