የፍርድ አሰጣጥና ፍትህን ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አዘጋጅነት “ፍርድ ቤቶች ከየት ወዴት” የሚል ሲምፖዚየም አካሄዱ፡፡

በሲምፖዚየሙ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት መዓዛ አሸናፊን ጨምሮ ሌሎች የህግ ባለሙያዎች እና ዳኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ቀደም ሲል በፍርድ ቤቶች ይስተዋሉ የነበሩ የዳኝነት ገለልተኝነት፣ የፍርድ አሰጣጥ፣ ፍትሀዊነት ጉድለትን ጨምሮ በርካታ ተግዳሮቶች እንደነበሩባቸው ያነሱት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት መዓዛ አሸናፊ አሁን ላይ ተግዳሮቶችን ነቅሶ በማውጣት በርካታ ማሻሻያዎችን በማድረግ የፍርድ አሰጣጥ ስርአቱንም ሆነ ፍትህን ለማረጋገጥና አመርቂ ውጤት ለማምጣት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የህግ ማዕቀፎችንም ከሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማገናዘብ ከህዝቡ ጥያቄ ጋር የተጣጣመ መሆን እንደሚገባ በመድረኩ ተመላክቷል፡፡

(በሄብሮን ዋልታው)