የፓውንድ መግዛት አቅም ከዶላር አንጻር ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ዝቅ አለ

መስከረም 16/2015 (ዋልታ) ከአውሮፓውያኑ 1971 በኋላ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ የዩናይትድ ኪንግደም ፓውንድ ከአሜሪካ ዶላር ጋር ሲነጻጸር ያለው ዋጋ ማሽቆልቆሉ ተነገረ።

ፓውንድ ስተርሊንግ በእስያ ገበያ ያለው የመግዛት አቅም በ4 በመቶ የወረደ ሲሆን አንዱ ፓውንድ ዋጋ ቀደም ሲል ከነበረው ከ1.05 ወደ 1.0327 ዶላር ዝቅ ብሏል።

ይህ የተሰማው የዩናይትድ ኪንግደም ቻንስለር ካዋሲ ከዋርቴነግ በከፍተኛ የብድር ድጋፍ የታገዘ ታሪካዊ የታክስ ቅነሳን ይፋ ካደረጉ በኋላ ነው።

በአሜሪካ ማዕከላዊ ባንክ እየተደረገ ያለው ዶላርን የማጠናከር እና የወለድ ምጣኔ ጭማሪ የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ፓውንድ ከዶላር አንጻር ያለው የመግዛት አቅም ጫና ውስጥ እንዲገባ ምክንያት ሆኗል።

በተጨማሪም ከዶላር አንጻር የዩሮ የመግዛት አቅም ከ20 ዓመት ወዲህ በእስያ ገበያ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ዝቅ ብሏል።

ይህም በዩክሬን የተቀሰቀሰው ጦርነት ያስከተለው የነዳጅ ቀውስ መቼ እንደሚፈታ ምልክት አለማሳየቱ ባለሃብቶችን አሳስቧል ተብሏል።

በአሁኑ ወቅት ሁሉም የመገበያያ ገንዘብ አይነቶች ከዶላር አንጻር ያላቸው አቅም እየተዳከመ ሲሆን የአሜሪካ ዶላር ከፍተኛ ጥንካሬ እያሳየ መሆኑን የቢቢሲ ዘገባ አመላክቷል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW