ያለፉት አምስት ወራት የሰላም ተስፋ የሰነቅንበት ነበር – አምባሳደር ሂሩት ዘመነ

መስከረም 7/2015 (ዋልታ) ያለፉት አምስት ወራት በኢትዮጵያ የተጀመረው የሰላም ሂደት በስኬት ይጠናቀቃል የሚል ተስፋ የሰነቅንበት ነበር ሲሉ በብራሰልስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ገለጹ።

አምባሳደር ሂሩት ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ በሚመለከት ብራሰልስ ታይምስ በተሰኘ ጋዜጣ ሰፋ ያለ ጽሁፍ አቀርበዋል።

በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል አሸባሪው ቡድን በከፈተው ጦርነት የወደሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለመግንባት የኢትዮጵያ መንግስት 2 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ወጪ ማድረጉን አምባሳደር ሂሩት በጽሁፋቸው ጠቁመዋል።

በተጨማሪም መንግስት በትግራይ ክልል የተቋረጡ መሰረታዊ አገልግሎቶችን ለማስጀመር የተቻለውን ሁሉ አድርጎ እንደነበር ገልጸዋል።

ይህ ሁሉ የመንግስት ሆደ ሰፊነት ለሰላም ቅድሚያ ለመስጠት ቢሆንም አሸባሪው ቡድን ግን የሰላም አማራጭን ወደጎን ማለቱን አንስተዋል።

ይህንንም ነሐሴ 18 ቀን 2014 ዓ.ም በአፋርና አማራ ክልሎች ሶስተኛ ዙር ጥቃት በመክፈትና ወረራ በመፈጸም ለሰላም ዝግጁ አለመሆኑን በድጋሚ ማረጋገጡን አምባሳደር ሂሩት በጽሁፋቸው አስረድተዋል።

በነስረዲን ኑሩ