ገንዘቤ ዲባባ በስፔን ባርሴሎና የተደረገው የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድር አሸነፈች

አትሌት ገንዘቤ ዲባባና ታናሽ እህቷ አና ዲባባ በስፔን ባርሴሎና የተደረገው የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድርን 1ኛና 2ኛ ደረጃ በመያዝ አሸንፈዋል፡፡

ገንዘቤ ውድድሩን ለመጨረስ የፈጀባት ጊዜ 15:00 ሲሆን፣ አና ዲባባ ደግሞ 16:02 በሆነ ጊዜ ውድድሩን አጠናቃለች፡፡