ጋዜጤኛ ሲሳይ ፊዳ በሸኔ ታጣቂዎች ተገደለ

ግንቦት 02/2013 (ዋልታ) – የኦቢኤን ጋዜጠኛ ሲሳይ ፊዳ በትላንትናው ዕለት በሸኔ ታጣቂዎች መገደሉን የቄለም ወለጋ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡

ጋዜጤኛ ሲሳይ በመኖሪያ ቤቱ አካባቢ በ11፡30 በሁለት የሸኔ ታጣቂዎች የግድያ ወንጀሉ መፈፀሙን በቄለም ወለጋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የአካባቢ ሰላም አስከባሪ ምክትል ዳሬክተር ኢንስፔክተር አህመድ ያሲን ለኦቢኤን ገልፀዋል፡፡

የወንጀሉ ፈፃሚዎች ማንነት በቅርብ ክትልል እየተደረገ መሆኑን ኢንስፔክተሩ ገልፀዋል፡፡

ጋዜጠኛ ሲሳይ መልካም ሥነ ምግባር ያለው እና ለህዝብ ሀቅ በትጋት የሚሰራ ጠንካራ ጋዜጠኛ ነበር፡፡

ዋልታ ሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን ኮርፖሬት ለጋዜጠኛ ሲሳይ ፊዳ ቤተሰቦች፣ ወዳጆች እና ለስራ ባልደረቦቹ መፅናናትን ይመኛል፡፡