አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ በ10ሺህ ሜትር ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸነፈች

ግንቦት 02/2013 (ዋልታ) – አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ በፖርቹጋል በተደረገ የፌርናንዳ ሪቤይሮ ጎልድ ጋላ በ10 ሺህ ሜትር ሴቶች ውድድር ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸነፈች፡፡
አትሌት ጉዳፍ በኢቨንቱ የመጀመሪያ ተሳትፏ 29፡39.42 የሆነ ሰዓት በመሮጥ የዓለም የምንጊዜም 5ኛውን ፈጣን ሰዓት አስመዝግባለች፡፡
በመሆኑም ርቀቱን ያሸነፈችበት ሰዓት አትሌት አልማዝ አያና በሪዮ 2016 ኦሊዮምፒክ ካስመዘገበችውና የዓለም ሪከርድ ከሆነው 29:17.45 ሰዓት በመቀጠል በኢትዮጵያ የርቀቱ ሁለተኛዋ ፈጣን ሴት አትሌት እንደሚያደርጋትም ከአፍሪካ አትሌቲክስ ዩናይትድ ማህበራዊ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡