ግብፅና ሱዳን በህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚያደርጉትን ትንኮሳ ሊያቆሙ ይገባል – የኢትዮጵያ ነፃነት ፖርቲ

የኢትዮጵያ ነፃነት ፖርቲ

ግንቦት 09/2013 (ዋልታ) – ግብፅና ሱዳን በህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚያደርጉትን ትንኮሳ ሊያቆሙ ይገባል ሲል የኢትዮጵያ ነፃነት ፖርቲ አሳሰበ፡፡

ፖርቲው ዛሬ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጠው መግለጫ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከዳር መድረሱ የሚያንገበግባቸው ግብፅና ሱዳን በህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚያደርጉትን ትንኮሳ ሊያቆሙ ይገባል ብለዋል።

የፖርቲው ሊቀመንበር አቶ ግዛቸው አመራ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ከመተባበር ይልቅ በሴራና በተንሸዋረረ ዲፕሎማሲ ጫና ለመፍጠር የምትታተረው ግብፅ ግልፅ ሴራዋን ልታቆም እንደሚገባ ገልጸዋል።

አቶ ግዛቸው አክለውም የህዳሴ ግድቡ ከፖለቲካ በላይ በመሆኑ ለፖለቲካ ፎጆታ የሚውል እንዳልሆነ  አመላክተዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብም የሀገሪቷን እድገት ለማይሹ ሀይሎች ማስፈፀሚያ ከመሆን ይልቅ በአንድነት በመሆን ግድቡን ከዳር ማድረስ ይገባል ብለዋል።

(በዙፋን አምባቸው)