ጎህ ቤቶች ባንክ ሥራ ጀመረ

ጥቅምት 15/ 2014 (ዋልታ) ጎህ የቤቶች ባንክ ሥራ ጀመረ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማዋ የቤት አቅርቦት እና ፍላጎትን ለማሟላት መንግሥት የተለያዩ ተግባራትን በመንደፍ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመፍታት መንግሥት ብቻውን በቂ አይደለም ያሉት ከንቲባዋ በመኖሪያ ቤት ግንባታ ዘርፍ የሚሰማሩ እንደጎህ የቤቶች ባንክ እና መሰል የፋይናንስ ተቋማት ሊበራከቱ ይገባል ብለዋል።
ባንኩ ውጤታማ እንዲሆን እና የታለመለትን ዓላማ እንዲያሳካ የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ከንቲባዋ አመልክተዋል።
የጎህ ቤቶች ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሙሉጌታ አስማረ በበኩላቸው ከቤት ፋይናንስ ጋር በተያያዘ ያለውን ክፍተት በመረዳት መፍትሄ ለማምጣት የተቋቋመ የመጀመሪያው የቤቶች ባንክ ነው ብለዋል።
የከተማ አስተዳደሩ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎችን ቤት ለማደስ የጀመረውን እንቅስቃሴ ለማገዝም የ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሰክሪታሪያት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!