ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት ተማሪዎቹን አስመረቀ

ሐምሌ 23/2013 (ዋልታ)-ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 6ሺህ 564 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመረቀ።

ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ፣ በስፔሻሊቲ እና በተለያዩ የትምህርት መርሃ ግብሮች ያስተማራቸውን 6 ሺህ 349 ተማሪዎች ነው በዛሬው ዕለት የሚያስመርቀው፡፡ የተቀሩት 225ቱ በመማር ማስተማር ስነ ዘዴ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ መምህራን ናቸው፡፡

ከተመራቂዎቹ መካከል 4 ሺህ 153ቱ ወንድ ተማሪዎች ሲሆኑ 2ሺህ 421 ሴቶች ናቸው፡፡

ዶ/ር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ የዕለቱ የክብር እንግዳ ናቸው::

ባሳለፍነው ሐሙስ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት የድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁንን የክብር ዶክትሬት ማፅደቁ ይታወሳል። ቴዎድሮስ በዛሬው የምርቃት ስነ ስርዓት ላይበመገኘት የክብር ዶክትሬቱን የሚረከብ ይሆናል፡፡

አንጋፋው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በአሁን ሰዓት በ27 የትምህርት ፕሮግራሞች ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ ይገኛል፡፡

(በሳሙኤል ሀጎስ)