ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ደቡብ ሱዳን ገቡ

መጋቢት 4/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ደቡብ ሱዳን ጁባ መግባታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ደቡብ ሱዳን ጁባ ከተማ ሲደርሱ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት ነው ደቡብ ሱዳን የገቡት።