የጮቄ ተራራ ኢኮ ቱሪዝም ልማት የዓለም ድንቅ ቱሪዝም መንደር ውድድር አሸናፊ ሆነ

መጋቢት 4/2015 (ዋልታ) በአማራ ክልል በጎጃም ዞን የሚገኘው የጮቄ ተራራ ኢኮ ቱሪዝም ልማት የዓለም ድንቅ ቱሪዝም መንደር ውድድርን አሸንፏል፡፡
በኢትዮጵያ ሦስተኛው ከፍተኛ ተራራ የሆነው ጮቄ ተራራ ላይ የሚገኘው የቱሪዝም መንደር በዋናነት ለገጠር ልማት አንቀሳቃሽ እንደሚሆን ይገለጻል፡፡
በተባበሩት መንግስታት የዓለም ቱሪዝም ድርጅት ይህንን የጮቄ ተራራ ኢኮ ቱሪዝም ልማት የዓለም ድንቅ ቱሪዝም መንደር ውድድር አሸናፊ አድርጎ መርጧል።
የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ ሽልማቱን ከጮቄ ሙሉ ኢኮ ሎጅ ተወካዮች ጋር በሳዑዲ ዓረቢያ አሉላ ከተማ ተቀብለዋል።
በውድድሩ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ50 በላይ ሀገራት እና ከ100 በላይ የቱሪዝም መዳረሻዎች መሳተፋቸውን ከቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
በሽልማት ስነ ስርዓቱ ላይ በሳውዲ ሀገር የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሌንጮ ባቲ ተገኝተዋል፡፡