ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለዲፕሎማቶች ስልጠና ሰጡ

ኅዳር 14/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት በአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ በመገኘት ለኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ስልጠና ሰጥተዋል።

በዚህም አዲሱን የሀገሪቱ ዲፕሎማሲ አካሄድ ፣ በሂደቱ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች  እና ቀጣይ አቅጣጫዎችን በተመለከተ ገለፃ ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።