ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሩሲያ-ቅዱስ ፒተርስበርግ ከተማ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ቅዱስ ፒተርስበርግ ከተማ ሲገቡ የተደረገላቸው አቀባበል

ሐምሌ 19/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሁለተኛው የሩሲያ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ ሩሲያ-ቅዱስ ፒተርስበርግ ከተማ ገብተዋል።

ፒተርስበርግ እንደደረሱም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ሕይወታቸውን ላጡ በ’ሌኒንግራድ ጀግኖች ተከላካዮች መታሰቢያ ሐውልት’ ላይ አበባ ጉንጉን አሳርፈዋል።