ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በሁለትዮሽ ጉዳይ ላይ ተወያዩ

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እና የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን

ሐምሌ 19/2015 (ዋልታ) በሩስያ አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ ፒተርስበርግ ከተማ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በሁለትዮሽ ጉዳይ ላይ ተወያዩ።

መሪዎቹ ባደረጉት ውይይት በሩስያ እና አፍሪካ መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ትብብር ለማጠናከር ተስማምተዋል።

በተጨማሪም በግብርና እና በንግድ ዘርፎች በጋራ ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት አረጋግጠዋል።

መሪዎቹ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ያደረጉት ውይይት ስኬታማ እንደነበርም ተገልጿል።