ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሱዳን ተቀናቃኝ ኃይሎች መሪዎች ጋር በስልክ ተወያዩ

ሚያዝያ 20/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሱዳን ጦር ኃይሎች መሪ ጄኔራል አብደልፈታህ አልቡርሃን እና ከሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መሪ ጄኔራል ሞሐመድ ሐምዳን ደጋሎ ጋር በስልክ መወያየታቸውን ገለጹ።

ታላቁ የሱዳን ሕዝብ ሰላም ያስፈልገዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሁለቱ መሪዎች ልዩነቶቻቸውን በመግባባት እንዲፈቱ እና ለሀገራቸው መረጋጋትን ማምጣት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን ገልጸዋል።