ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኬንያ ናይሮቢ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ

የካቲት 19/2016 (አዲስ ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለሁለት ቀናት መንግሥታዊ ጉብኝት ኬንያ ናይሮቢ ገቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኬንያ ናይሮቢ ሲደርሱ በጆሞ ኬንያታ አውሮፕላን ጣቢያ በፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በመቀጠልም ፕሬዝዳንት ሩቶ የወጣቶችን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ተሳትፎ የሚያሳይ የአይሲቲ ፓርክ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ማስጎብኘታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።