ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የተለያዩ ሹመቶችን ሰጡ

                        አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆኑ

ጥር 30/2016 (አዲስ ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው እለት የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል፡፡

በዚህም መሰረት ፡-
1. አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን – የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር
2. ትዕግስት ሃሚድ – የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር በመሆን ተሹመዋል፡፡
     ትዕግስት ሃሚድ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ