ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የእንኳን ደስ አልዎ መልዕክት አስተላለፈ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት

መስከረም 5/2015 (ዋልታ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የ2022 የዓለም አቀፍ ኢስላማዊ ፋይናንስ አዋርድ በማሸነፈቸው የእንኳን ደስ አልዎ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የ12ኛውን የዓለም አቀፍ ኢስላማዊ ፋይናንስ አዋርድ (GIFA) ሽልማት ተቀብለዋል።

ምክር ቤት በማኅበራዊ ትስስር ገፁ ባሰፈረው መልዕክት “ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና መንግስታቸው በሀገራችን ኢትዮጵያ በፋይናንስ ዘርፋ ባካሄዱት ሰፊ ማሻሻያ የ2022 ዓለም አቀፍ ኢስላማዊ ፋይናንስ (GIFA) አዋርድ ተሸላሚ በመሆንዎ የእንኳን ደስ አልዎ መልዕክቱን ሲያስተላልፍ ደስታ ይሰማዋል” ብሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዘንድሮው ተሸላሚ የሀገር መሪ ሆነው ሽልማቱን ያሸነፉት በኢትዮጵያ ያለው የፋይናንስ ሥርዓት እንዲዳብር ላበረከቱት አስተዋፅኦ እንደሆነ ትናንት መዘገባችን ይታወቃል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW